የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ዓላማዎች

  • የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም በህዝቡ ውስጥ ሰርፆና ተግባራዊ ሆኖ መላው የአገራችን ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ
  • ሴቶች በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ በየደረጃው የልማት የዴሞክራሲና የሰላም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል
  • ሴቶች ህገ-መንግስቱ ያጎናፀፋቸውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በትክክል ስራ ላይ እንዲውሉ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ለመብታቸው እንዲታገሉ ማስቻል
  • የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የሴቶችን አቅም በመገንባትና የሴቶች እኩልነት የሚገድቡ ባህላዊና ልማዳዊ ተጽዕኖዎችን በመለየት ለሀገር ዕድገት እና በሴቶች ላይ የሚፈጠሩትን ተጽዕኖ በማስገንዘብ እንዲወገድ በማድረግ ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት እኩል እንዲሳተፉ
  • ሴቶች የፈጠራ ዝንባሌያቸው እንዲጎለብት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የስራ ባህላቸው ዳብሮ ስራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውን እና ሀገራቸውን ከድህነት ለማውጣት የሚታገሉ እንዲሆኑ ማድረግ
  • ሴቶች ህብረ ብሄራዊ አንድነታቸውን በመጠበቅ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል በማጎልበት በሀገራዊ ጉዳዬች ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል

የብልጽግና ሴቶች ሊግ መርሆዎች

  • ህዝባዊነት
  • ዳሞክራሲያዊነት
  • የህግ የበላይነት
  • ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት
  • ተግባራዊ እውነታ
  • ሀገራዊ አንድነትና ህብረ-ብሄራዊነት

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የሚከተሉት እሴቶች

  • እህታማማችንት
  • መካባበር መቻቻል
  • ህብረብሄራዊ አንድነት
  • የዜጎች ክብርና የስርዓት ፅታ እኩልነት
  • ነፃነት
  • እኩል ተሳትፎ ና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት